ተገላቢጦሽ

January 31st, 2009

ተገላቢጦሽ

በሃገር ቤት ሳለን ….

ኩታ ከደራረበው መሀል - እርቃኑን ሲሄድ ብናየው
አንጀታችን ቢላወስ - አበደ ለየለት አልነው
አይሰማ የለ ዛሬ - ይኽው ደርሰን ከውጭ ሃገር
ለቅፅበት ላፍታ ያህል - ድንገት ብትወጣ ጀንበር
እርቃኑን ከተመመው መሀል - ብንታይ ኩታ ደርበን
ከእብዶች ጎራ ፈረጁን - ዘመኑ ይህን አሳየን

ወይ ጉድ …….!

በትሩዝ የተገጠመ!


961 Comments »

ቋንቋ

January 31st, 2009

ቋንቋ

ቁም ነገር አጭቆ ካላስተላለፈ
ሁሉን አነባብሮ በ‘ኩል ካላቀፈ
ቋንቋ ምን ሊፈይድ ለወሬ ከዋለ
በብሄር ከፋፍሎ ሰውን ካጋደለ ?

ሊጠቃቀም እንጂ ያዳም ዘር በሙሉ
ሊከውን አጢኖ ሊሆን እንደቃሉ፤
ታንድ አልሞ እንዲጓዝ ካላስተሳሰረው
ቋንቋ ምን ሊረባ ካገር ካባረረው ?

ጭንቁር እየሆነ ሌላውን የመውጊያ
ጎጠኛ ካ‘ረገው ላያይ ከርሱ በስቲያ፤
አልያ ችንካር ሆኖ እያደናቀፈው
አቂሞ ለመጥላት አቅምን ከቸረው
ይቅር ምን ሊጠቅም—ቋንቋ ምን ዋጋ አለው ?

በትሩዝ የተገጠመ::

“ለመጣላትም እኮ መጀሪያ መግባባት ያስፈልጋል” ከሎሚ ኮፒ የተደረገ!


250 Comments »

ቀድሞ ነበር እነጂ

January 31st, 2009

ከጀርባው ላይ

ተበድሮ ተለቅቶ
ታናሽ ታላቅ ስጋ ገዝቶ …
ድል ! አድርጎ በመደገስ
ሲንጎራደድ በመኮፈስ …

በድንገት… ..

ሙዳ ስጋ እያስመተረ ፣ እንደሚያሻው
ከሽንጡ ዳር ተሰልፎ ፣ ህዝቡን ቢያየው (ወይኔ ወንድሜን )

ላፍታ ያህል…

የገባበት የእዳ መአት ፣ ትዝ ሲለው
ከትከሻ፤ ከጀርባው ላይ ፣ የሚበልቱት መሰለው፡፡

ቀድሞ ነበር እነጂ… አለ ያገሬ ሰው

በትሩዝ የተገጠመ!


287 Comments »

አያድርስ

January 31st, 2009

አያድርስ

በፍቅርህ ሞቻለሁ ስትይኝ ሳልም ደረቴን ስደቃ
አገባሁሽ ብዬ ሃሴት ሳደርግ - ለካ ሰመመን ነው ስነቃ
በሚዜዎች ታጅበን - ከጫጉላ ቤት ስንገባ
እሱም በህልሜ ሆነና አረፈው - በንዴት ታጠብኩልሽ በእንባ

ወይ ስቃይ ….

ምን አለበት እሺ ብለሽኝ ከጭንቀት ብትገላግይኝ
በቀን ቅዠት በለሊት ህልም መጥተሽ ባታስጨንቂኝ”
በማለት አጭር ደብዳቤ - ጉርድ ፎቶዬን አክዬ
ማለፍያ ፊደላትን ቀምሬ - ልብሽን ይነካ እንደሁ ብዬ
ላቀብልሽ በርሽ ላይ ብውል - አልወጣ ብትይ ወደ ቀዬ
መቼም ፍቅር ይዞኛልና…… መመለስ ቢያቅተኝ ችዬ
አመድ ለብሰው ከሚራወጡት - ከመንደሩ ኩታራ መሃል
ደብዳቤውን ስጥልኝ አልኩት - መክሬ እንዲያመጣልኝ ባይቻል

ለካ ከራሱ የተጣላ ዱርዬ - ከይሲ … ተንከሲስ ኖሯል
አደራ አድርስልኝ ያልኩትን - እሱ ለእናትሽ ሰጠቷቸዋል ::
እሳትጎርሰው ወጡ እናትሽ - እንደ ጨበጡ ጠብደልድንጋይ
ከትቢያ ሊደባልቁኝ - ሊደሰቱ በእኔ ስቃይ

በቆምኩበት ደርቄ ቀረሁ እንደ እንጨት ክው ብዬ
ስለት ላምላኬ እየገባሁ ህልም እንዲያደርገው አንድዬ
ስንተቃቀፍ ህልም ካረገው - የፀቡ አይሳነውም ብዬ።

እውነት::


1010 Comments »

ግን ማን ናት ?

January 31st, 2009

ግን ማን ናት ?

ከግድግዳው ላይ ተሰቅሎ - ለአፍታ ብታየው ምስሏን
እርስዋ እንዳልሆነች ገለጠው - በማስታወስ ማንነቷን
ለካስ ፎቶ አንሽው ኖሯል - ፈገግ በይ ያምራል ያላት
እሷነንቷን እንዳትገልጠው - ለራሱ ገበያ የሳላት

እውነት::


210 Comments »

ትለምጂዋለሽ

September 11th, 2008

ትለምጂዋለሽ አሉኘ ነገሩን አቅልለልው

የሀገሬን ፍክር የቤተሰብ ፍክር በከላሉ አይተው

አረ ወገኖቺ እስቲ እንነጋገር

ባሕር ማዶ መኖር የመልመጃው ምስጢር

ትለ

በምስር ክክ የተግጠመ


1020 Comments »

ቲማቲም

May 8th, 2008

ከቲማቲም የተዘጋጁ ምግቦችን በየቀኑ መመገብ ለቆዳ ጤንነት ጥሩ እንደሆነ አዲስ በተካሄደ ጥናት ተረጋገጠ፡፡ ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት ፒዛ እና ስፓጌቲም ቆዳ በፀሃይ እንዳይቃጠልና በእርጅና ምክንያት የሚከሰትን የቆዳ መሸብሸብ ለመከላከል ያስችላሉ፡፡

በየቀኑ አምስት የሾርባ ማንኪያ ቲማቲም ምግባቸው ጋር እየቀላቀሉ በሚጠቀሙ 1ዐ ያህል በጎፈቃደኛ ሰዎች ላይ የተደረገው አዲሱ ጥናት ቲማቲም ለጤና አደገኛ የሆነውን የአልትራ ቫዮሌት የፀሃይ ጨረር የመከላከል ብቃቱ እንዲጨምር አድርጓል፡፡

በተጠቀሰው የፀሃይ ጨረር መቃጠል ያለ እድሜ የቆዳ መሸብሸብንና የቆዳ ካንሰርንም ሊያስከትል ይችላል፡፡

ከዚህ በፊት የተደረገ አንድ ጥናት ቲማቲም በወንዶች ላይ የሚከሰተውን የኘሮስቴት ካንሰር መቀነስ እንደሚችል የሚያረጋግጥ ነበር፡፡ አሁን በማንችስተርና ኒውካስትል ዩኒቨርሲቲዎች የተካሄደው አዲሱ ጥናት ደግሞ አደገኛውን የአልራ ቫዮሌት ጨረር እንዲቋቋም ቆዳን በመርዳት የቆዳን ጤንነት መጠበቅ እንደሚችል የሚያሳይ ነው፡፡

ተመራማሪዎቹ ለቆዳ ጤንነት የሚጠቅሙ ምግቦች ብለው ከገመቷቸው መካከል በወይራ ዘይት ላይም ጥናት አድርገዋል፡፡ 2ዐ ያህል በጎ ፈቃደኞችን እንደ ናሙና በመውሰድ 1ዐ የሚሆኑት 55 ግራም የበሰለ ቲማቲም እንዲወስዱ ተደረገ፤ ቀሪዎቹ ደግሞ 1ዐ ግራም የወይራ ዘይት በየቀኑ ወስደዋል፡፡ ከሦስት ወር በኋላ ከሁለቱም ቡድን የቆዳ ናሙና ተወስዶ በተረገላቸው ምርመራ ቲማቲም ተመጋቢዎች 33 በመቶ በፀሃይ የመቃጠል አደጋን የቀነስላቸው ሲሆን የወይራ ዘይቱም ለቆዳ ጤንነት አስተዋፅኦ እንዳለው ታውቋል፡፡ ተመራማሪዎቹ “ቲማቲም መመገብ ከፀሃይ መከላከያ ክሬም ትንሽ ባነሰ መልኩ ቆዳን ከፀሃይ ጉዳት የሚከላከል ቢሆንም ጨርሶ የፀሃይ መከላከያ ክሬምን መጠቀም ማቆም አያስፈልግም፡፡ ቲማቲምን እንደ አጋዥ መጠቀም ተገቢ ነው” ሲሉ አሳስበዋል፡፡


73 Comments »

ናፍቆት

April 8th, 2008

በእኔና አንቺ መሀል ወንዝ አለ መራራ፣
አላገናኝ አለኝ፣ ሆኖኝ ባላጋራ፤
ያዘኝ ደሀነቴ ድልድይ እንዳልሠራ፣
ዋኝቼ እንዳልመጣ ውሀ ልቤ ፈራ፡፡
አንቺ ወዲያ ማዶ፣ እኔ ወዲህ ማዶ፤
ልባችን በስሜት ርቀቱን ጥሶ፣ ገደሉንም ንዶ፤
ልዩነት ጅረትም ፈሶ፤ ወርዶ፤ ወርዶ፤
ቀን ሳይሞላ አይቀርም ለኛ ተዋኅዶ፡፡
እስቲመቸኝ ድረስ፣ እስቲመችሽ ድረስ እስከዚያ ልጨነቅ፤
እስቲመጣ ጊዜ ያንን ወንዝ የሚያደርቅ፣
የስሜቴን ምሥጢር እስተዚያ ልደብቅ፣
ያንን ፈገግታሽን እነዚያ ዓይኖችሽን በናፍቆት ልጠብቅ፡፡

መስፍን ወልደ ማርያም፤ እንጉርጉሮ፣ 1967
* * *


1034 Comments »

አባባሎች

February 26th, 2008

- ደስ መሰኘትና መከፋት ሲዘዋወሩ ስለሚኖሩ ደስ ያለው እንደሚከፋው፣ የከፋው ደስ እንደሚለው አይጠረጠርም፡፡
- በዕድሜ መሰንበትና ፈተናን ሁሉ አልፎ ወደ ደህና ቀን መድረስ ብዙ ጊዜ መታደልና መክበር ነው፡፡
- በእናት ማኅፀን የተፀነሰ ፅንስ ቀኑ ሲደርስ በማኅፀን ታግዶ እንደማይቀር ሥራም በትጋት ከተጀመረ የሠራተኛው አሳብ ከወሰነው ጊዜ አያልፍም፡፡
- ፍልስፍና አድራሻ የለውም፤ ያለ ዕረፍት ሲሄድ የሚኖር የምርመራ አሞራ ከመሆኑም የተነሳ ከሁሉ ይደርሳል፡፡
- ማወቅ ወጣም ወረደ ለመደነቅ ብቻ አይደለም፤ ስህተት የሌለበት ሙሉ ሰውን ለመሆንም ነው እንጂ፡፡
- ሥጋ በመንፈስ እየተንቀሳቀሰ፣ መንፈስ በሥጋ እየተዳበሰ ግዙፍነትንና ረቂቅነትን ለመግለጽ፣ መንፈስ ወደ መንፈሳዊነት፣ ሥጋም ወደ ሥጋዊነት እያዘነበለ፣ በአንድ ሰው አካል ሁለት ኃይል ሲሠራ ይኖራል፡፡

(ብላታ ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስ፣ 1935)


241 Comments »

ቤት የማይመታ ግጥም

February 26th, 2008

ቤት የማይመታ ግጥም

ሕገ ወጥ ቤት፡- አካሄዱ ግጥም ሲመስል ቤት የሚያፈርስና የግጥሞችን ሕግ የማይጠብቅ ነው፡፡ እንደዚህ ያለው ግጥም በድሮ ዘመን በባላገሮች ዘንድ ይነገር ነበር፡፡ በአሁኑ ዘመን ግን እንደ መሳቂያ እንጂ ለሥራ አያገለግልም፡፡

አትለው ሞይ /ማጅር ማጅሩን
አንተ ምንቸገረህ /እሱን ታላመመው፡፡
የማነው በሬ /እግዜር የማረው፡፡
እቅብቅብ ገብቶ /ይነፈንፋል፡፡
ከኔውም እንደሆን /ተውቃቢዬ፡፡
ሎሚ ስይዘው/ ይሸትብኛል፡፡
ያውና እዚያ ማዶ /ቃሪያ በርበሬ፡፡
ባደረ እንጀራ /ቢኮሸኩሹት፡፡
ዝናብ ዘንቦ ዘንቦ /ደጁ ጭቃ ነው፣
ያንን ያነሱ /እግድግዳ ልጥፍ፡፡
እንዲህ ብታየኝ /መስዬህ ድኃ፣
ያማቶቼ ቤት /ባለጉልላት፡፡
የጦጣ ጅራት /ከወደኋላዋ፣
ሐሰቴንም እንደሁ /ዞረህ እይብኝ፡፡
አፋፍ ላፋፍ ስሄድ /አገኘሁ ሚዳቋ፣
ጅራቷን ብይዛት /ዓይኗ ፍጥጥ አለ፡፡

(መርስዔ ኅዘን ወልደቂርቆስ፣ የአማርኛ ሰዋሰው፣ 1935)


315 Comments »

Next Page »